እኛ የፀረ-መድልዎ ሕግ (Anti-Discrimination Act) 1977 (ሕጉ) የሚያስተዳድር የኒው ሳውዝ ዌልስ የመንግስት አካል ነን። እኛ ነፃ አገልግሎቶችን እናቀርባለን እና በኒው ሳውዝ ዌልስ አድልዎ ለማስወገድ የሚከተለው በማድረግ እንጥራለን፦
መድልዎ ማለት አንድ በኒው ሳውዝ ዌልስ ህግ መብቱ የተጠበቀ ባህሪ ያለው ሰው ወይም አለው ተብሎ በሚገመት ሰው ላይ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሲስተናገድ ነው።
እነዚህ ባህሪያት የሚከተሉት ናቸው፦
በአንዳንድ የህዝብ ቦታዎች መድልዎ መፈጸም ከህግ ውጪ ነው። እነዚህም ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
የተንከባካቢ ሃላፊነት መድልዎ በስራ ቦታ ላይ ብቻ ነው ከህግ ጋር የሚጻረረው።
አንድን ሰው ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ማድረግ ከህግ ውጪ ነው። ጾታዊ ትንኮሳ ማለት አንድ ሰው ቅር እንዲሰኝ፣ እንዲዋረድ ወይም እንዲሸማቀቅ የሚያደርግ ማንኛውም የማይፈለግ ወሲባዊ ተፈጥሮ ያለው ባህሪ ነው።
ይህም የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦
ማንቋሸሽ/ስድብ በአንድ ሰው ወይም ቡድን ላይ ጥላቻ፣ ከባድ ንቀት ወይም መሳለቅ የሚያነሳሳ ህዝባዊ ድርጊት ነው። አንዳንድ ባህሪያትን ማንቋሸሽ ከህግ ጋር ይቃረናል።
እነዚህ ባህሪያት የሚከተሉት ናቸው፦
በዘራቸው፣ በሃይማኖታቸው ወይም በዝምድናቸው፣ በፆታ ዝንባሌያቸው፣ በጾታ ማንነታቸው፣ በጾታቸው፣ ከሁሉም ጾታዎች ጋር ግንኙነት ወይም ኤችአይቪ/ኤድስ ስላላቸው በዚህ ምክንያት አንድን የማኅበረሰብ ክፍል የሚያስፈራራ ወይም ብጥብጥ የሚያነሳሳ ማንኛውም ህዝባዊ ድርጊት ለፖሊስ መቅረብ ያለበት የወንጀል ድርጊት ነው።
የመድልዎ ቅሬታ ስላቀረቡ (ወይም ለማቅረብ ስላቀዱ)፣ ወይም ስለ አድልዎ ቅሬታ መረጃ ወይም ማስረጃ ስላቀረቡ ግፍ ከተፈፀመብዎት፣ ይህ ሰለባ ማድረግ በመባል ይታወቃል። በኒው ሳውዝ ዌልስ ሰለባ ማድረግ ከህግ ጋር የሚጋጭ ነው።
የፀረ-መድልዎ ኒው ሳውዝ ዌልስ መጠየቂያ አገልግሎትን በስልክ ቁጥር 02 9268 5544 ወይም 1800 670 812 ይደውሉ ወይም ወደ adbcontact@justice.nsw.gov.au ኢሜይል ይላኩ። ሁኔታዎ ወይም በእርስዎ ላይ የደረሰው ነገር ህጉን የሚጻረር ስለመሆኑ እርግጠኛ ባይሆኑም ወይም ስለ ኒው ሳውዝ ዌልስ የፀረ-መድልዎ ህጎች አንዳንድ መረጃ ከፈለጉ እኛን ማግኘት ይችላሉ።
መድልዎ፣ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ማንቋሸሽ/ስድብ ካጋጠመዎት እና ስለ አንድ ሰው ወይም ኩባንያ መደበኛ ቅሬታ ማቅረብ ከፈለጉ፣ እባክዎን የቅሬታ ቅጹን ይጠቀሙ። ቅሬታዎን በማንኛውም ቋንቋ መጻፍ ይችላሉ፣ እና ቅሬታዎን ያለምንም ክፍያ ወደ እንግሊዝኛ እንተረጉማለን። ቅሬታዎን ወደ complaintsadb@justice.nsw.gov.au ኢሜል ያድርጉ። ቅሬታዎን ለመጻፍ ለእርስዎ አስቸጋሪ ከሆነ፣ ቅሬታዎን ለማቅረብ የሚያስችሉ ሌሎች አማራጮችን ለመወያየት እኛን ማግኘት ይችላሉ።
ማናቸውንም አገልግሎቶቻችንን ለማግኘት አስተርጓሚ ከፈለጉ፣ እባክዎን ወደ የትርጉም እና አስተርጓሚ አገልግሎትን በ 131 450 ይደውሉ እና ወደ ፀረ-መድልዎ ኒው ሳውዝ ዌልስ በ 02 9268 5544 እንዲደውሉ ይጠይቋቸው።
የህግ እርዳታ ከፈለጉ፣ ወደ የህግ መዳረሻ (Law Access) በስልክ ቁጥር 1300 888 529 ይደውሉ።
በወንጀል የሚያስጠይቅ መድልዎ ወይም ማንቋሸሽ/ስድብ አጋጥሞዎት ከሆነ፣ እባክዎን የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስን ያነጋግሩ።
የኛ ሚና ሁለቱም አካላት፣ እርስዎ እና ሌላው አካል፣ መፍትሄ እንዲያገኙ መርዳት ነው። ቅሬታዎን ስንቀበል፣ ከህግ ጋር የሚጻረር ሁኔታ መስሎ ከታየን፣ ቅሬታዎን ወደሚቀጥለው ደረጃ እናደርሳለን።
ቅሬታዎ በደረሰን በሁለት ሳምንታት ውስጥ በስልክ ወይም በደብዳቤ እናገኝዎታለን። ከእርስዎ ጋር ስንነጋገር፣ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ሌላ መረጃ ልንጠይቅዎት እንችላለን። ቅሬታዎን እንዴት ልናስተናግድ እንዳቀድንም ከርስዎ ጋር እንወያያለን።
እርስዎ ቅሬታ ያቀረቡበት ሰው ምላሽ ሰጪ ይባላል። ለምላሽ ሰጪው ያቀረቡትን ቅሬታ ቅጂ እና ያቀረቡትን ማንኛውንም ወረቀት ስለሚመለከተው ህግ የሚያስረዳ እኛ ከጻፍነው ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን እንልካለን። ከዚያም ምላሽ ሰጪው ምላሽ የመስጠት እድል ይኖረዋል።
ይህ ሁኔታውን ካልፈታው፣ በእርስዎ እና በምላሽ ሰጪው መካከል ስብሰባ ልናደርግ እንችላለን። ይህ የእርቅ ጉባኤ ይባላል። እርቅ ሁለቱም ወገኖች አንድ ላይ ተሰባስበው ቅሬታውን ለመፍታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመወያየት እድል የሚሰጥ ነው።
ከርስዎ ጋር ልንወግን ወይም የሕግ ምክር ልንሰጥዎ አንችልም። ጉዳዩን እንዲፈቱ ልንረዳዎ ካልቻልን፣ ቅሬታዎን ወደ ኒው ሳውዝ ዌልስ የሲቪል ጉዳይ አስተዳደር ጉባኤ (NSW Civil and Administrative Tribunal) መውሰድ ይችሉ ይሆናል።
የአቤቱታ ቅጹን ያውርዱ። (DOCX, 1.8 MB)
28 Oct 2024
We acknowledge Aboriginal people as the First Nations Peoples of NSW and pay our respects to Elders past, present and future. We acknowledge the ongoing connection Aboriginal people have to this land and recognise Aboriginal people as the original custodians of this land.